Get Help (Amharic)

Choose Your Language:

               

የኢሚግሬሽን የሕግ አገልግሎቶች

 

ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ስደተኞች የኢሚግሬሽን ጉዳይ ላይ የሚሰጥ የሕግ ማማከር አገልግሎት እገዛ

የማማከር አገልግሎቶቹ የሚሰጡት በቀጠሮ ብቻ ነው።

በዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን የእኛን የዲሲ ቢሮ 202-387-4848 ላይ ደውለው ያግኙ።

በቨርጂኒያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን የእኛን የዲሲ ቢሮ 703-444-7009 ላይ ደውለው ያግኙ።

በሜሪላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን የእኛን የዲሲ ቢሮ 240-594-0600 ላይ ደውለው ያግኙ።

አዩዳ (Ayuda) በተቻለ መጠን ነፃ የሕግ ማማከር አገልግሎቶችን ለማቅረብ ይሰራል። በምናገኘው የእርዳታ ገንዘብ የተነሳ ለብዙ ግለሰቦች፣ የማማከር አገልግሎቶችን ጨምሮ፣ ነፃ የኢሜግሬሽን የሕግ ጥብቅና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ችለናል።

በነፃ ልናገለግልዎት የማንችል ከሆነ፣ የአዩዳ (Ayuda) የህግ ማማከር ክፍያ $100 ነው። ለመክፈል የማይችሉ ከሆነ፣ እባክዎን የአዩዳ የሕግ ክፍያዎችን ያለክፍያ ለመስተናገድ ጥያቄ ማመልከቻ ያስገቡ።

የኢሚግሬሽን ጉዳዩች ጠበቃ በሚፈልጉበት ሰዓት፣ ጠበቃ-ያልሆኑ ወይም “ኖታሪዮሶች” ከሆኑ የኢሚግሬሽን የሕግ አገልግሎቶችን መስጠት ከማይችሉ ሰዎች ይጠንቀቁ። የእርስዎ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ላይ የማጭበርበር ጉዳት ደርሶብኛል ብለው የሚያምኑ ከሆነ፣ እባክዎን Project END ን በ 202-552-3604 ላይ ያግኙ።

የቤት ውስጥ ጥቃት እና የቤተሰብ ሕግ ማማከር አገልግሎቶች

በዲሲ ውስጥ ከቤት ውስጥ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ወይም ሰላም የመነሳት ችግር ተጠቂዎች የሕግ እገዛ።

የዲሲ በአካል ቀርበው የሚሰተናገዱበት ክሊኒክ አዩዳ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ወይም ሰላም የመነሳት ችግር ተጠቂ ለሆኑ የዲሲ ነዋሪዎች ሰዎች በአካል ቀርበው የሚስተናገዱበት ክሊኒክ ያቀርባል።

በዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እናም የቤተሰብ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ወይም ሰላም የመነሳት ችግር ተጠቂ ከሆኑ እና የልጅዎን አሳዳጊነት፣ የልጅ ማሳደጊያ ተቆራጭ ገንዘብ፣ ፍቺ፣ የሲቪል ጥበቃ ትዕዛዝ፣ ወይም እንደ የአንድ ወንጀል ተጠቂ ባለመብትነትዎ የሕግ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በዚህ ይደውሉ (202) 387-4848፣ (833) 422-0005 ወይም በስራ ሰዓት ላይ የእኛ የዲሲ ቢሮ ላይ ብቅ ይበሉ።

የስራ ሰዓት:

  • 9:00 AM – 12:00 PM
  • 1:00 PM – 4:00 PM

በሜሪላንድ ውስጥ ከቤት ውስጥ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ወይም ሰላም የመነሳት ችግር ተጠቂዎች የሕግ እገዛ።

በሜሪላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እናም የቤተሰብ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ወይም ሰላም የመነሳት ችግር ተጠቂ ከሆኑ እና የልጅዎን አሳዳጊነት፣ የልጅ ማሳደጊያ ተቆራጭ ገንዘብ፣ ፍቺ፣ የጥበቃ ትዕዛዝ፣ ወይም እንደ የአንድ ወንጀል ተጠቂ ባለመብትነትዎ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በስራ ሰዓት ላይ (240) 594-0600 ላይ ይደውሉ።

 

የስራ ሰዓት:

  • 8:30 AM – 12:00 PM

  • 1:00 PM – 4:30 PM

ለተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ ሰዎች የማህበራዊ አገልግሎቶች

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ለተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ ሰዎች የማህበራዊ አገልግሎቶች

የመዝገብ (ኬዝ) አስተዳደር እና/ወይም ቴራፒ አገልግሎቶች ለስደተኛ ተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ እና ለወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ስደተኞች ይሰጣሉ። የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የልጆች ጥቃት ወይም ችላ መባል ተጠቂ የሆኑ ስደተኞች ለኬዝ አስተዳደር አገልግሎቶች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

 

በዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን በዚህ ይደውሉ (202) 387-4848፣ የጽሁፍ መልዕክት (833) 422-0005 ላይ ይላኩ ወይም ለበለጠ መረጃ የእኛ የደንበኛ ማስተናገጃ ሰዓታት፣ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ 9:00 am እስከ 4:00 ድረስ ይጎብኙን።

 

በጣም አጣዳፊ አደጋ ውስጥ ያሉ ከሆነ 9-1-1 ላይ ይደውሉ ወይም የብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ ስልክ መደወያ መስመር 1-800-799-7233 ላይ ይደውሉ።

በጀርጂንያ ውስጥ ለተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ ሰዎች የማህበራዊ አገልግሎቶች

የመዝገብ (ኬዝ) አስተዳደር እና/ወይም ቴራፒ አገልግሎቶች ለስደተኛ ተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ እና ለወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ስደተኞች ይሰጣሉ። የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና የልጆች ጥቃት ወይም ችላ መባል ተጠቂ የሆኑ ስደተኞች ለኬዝ አስተዳደር አገልግሎቶች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቨርጂኒያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን በ (703) 444-7009 ስልክ ቁጥር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከ 8:30AM እስከ 5:00PM ድረስ ይደውሉ።

በጣም አጣዳፊ አደጋ ውስጥ ያሉ ከሆነ 9-1-1 ላይ ይደውሉ ወይም የብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ ስልክ መደወያ መስመር 1-800-799-7233 ላይ ይደውሉ።

በሜሪላንድ ውስጥ ለተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ ሰዎች የማህበራዊ አገልግሎቶች

የመዝገብ (ኬዝ) አስተዳደር እና/ወይም ቴራፒ አገልግሎቶች ለስደተኛ ተጠቂዎች እና ከጥቃት ለተረፉ እና ለወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ስደተኞች ይሰጣሉ። የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሆኑ ስደተኞችም ለኬዝ አስተዳደር አገልግሎቶች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ሜሪላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ እባክዎን በ (240) 594-0600 ስልክ ቁጥር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከ 8:30AM እስከ 4:30PM ድረስ ይደውሉ።

በጣም አጣዳፊ አደጋ ውስጥ ያሉ ከሆነ 9-1-1 ላይ ይደውሉ ወይም የብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ ስልክ መደወያ መስመር 1-800-799-7233 ላይ ይደውሉ።

በእርስዎ ቋንቋ እገዛ ለማግኘት

 

በእርስዎ ቋንቋ እገዛ ለማግኘት

የዲሲ መንግስታዊ ቢሮ ወይም ኤጀንሲን በማንኛውም ሰዓት በሚጎበኙበት ሰዓት ነፃ የአስተርጓሚ አገልግሎትን የማግኘት መብት አለዎት።

በእርስዎ ቋንቋ ሰነዶችን የማግኘትም መብት አለዎት። በእርስዎ ቋንቋ እገዛ ያልተሰጥዎት እንደሆነ፣ የዲሲ ሰብዓዊ መብቶች ቢሮን http://ohr.dc.gov/ በ (202) 727-4559 ላይ ደውለው ያግኙ።

በእርስዎ ቋንቋ ከእርስዎ ጋር ለመስራት የሚሹ ነፃ አስተርጓሚዎች መጠቀም ያለባቸው በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ነፃ ጠበቃዎች፣ ማህበራዊ ሰራተኞች፣ የመብት ተከራካሪዎች አሉ።

ጠበቃዎት ወይም የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኛዎ በእርስዎ ቋንቋ እገዛ የማይሰጡ ከሆኑ፣ ነፃ አስተርጓሚ ለማግኘት ለመሞከር አዩዳን (Ayuda) በ (202) 243-7317 ላይ ይደውሉ።