በአሁኑ ወቅት የአዩዳ (Ayuda) መስርያ ቤቶች በሙሉ ለህዝብ ዝግ ናቸው ግን ለደንበኞቻችን አገልግሎት መስጠታችንን እንቀጥላለን

ስልክ ሲደወልልን እናነሳለን።

ዲሲ (D.C.) 202-387-4848

ቨርጂንያ (VA) 703-444-7009

ሜሪላንድ (MD) 240-594-0600

ቤተሰብን የሚመለክት ሕጋዊ ምክርና ማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚፈልጉና ቀደም ሲሉ ቀጠሮ የያዙ የወቅቱና የቀድሞ ደንበኞች፡ ከቤተሰብ ሁከትና ብጥብጥ (domestic violence ) የዳኑ ሰዎች፡ በሰው ንግድ (human trafficking )በደል ያለፉ ሰዎች፡ ወሲባዊ በደል( sexual assault) የደረሰባቸው ወይም ሰው የሚያደባባቸው (stalking) ግለሰቦች፡ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ ስልክ እንዲደውሉልን እናበራታለን።

በአሁኑ ወቅት፣ አዩዳ (Ayuda ) ለስደተኞች ምክር የመስጠት አገልግሎትን በተመለከተ አዲስ ቀጥሮ በመስጠት ላይ አይደለም። በተቻለ መጠን ግን ዌብሳይቱን አዳዲስ መረጃዎችን መመርያዎች ሲኖሩ ያድሳቸዋል።

በወቅቱ የምንሳጣቸውን አገልግሎቶች የሚመለከት መረጃ፡

  • በዲሲ (DC) የሚገኙ፡ ከሚከተሉት ጉዳዮች የዳኑ ሰዎች፡ ከቤተሰብ ሁከትና ረብሻ ( domestic violence)፣ ከወሲባዊ በደል (sexual assault)፣ እና/ ወይም ከድብያ የዳኑ ሰዎች ተጨማሪ የቤተሰብ ሕግ ምክርና ማህበራዊ አገልግሎቶች ቢያስፈልጋቸው፡ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 9:00 እስከ ቀኑ 4:00 ድረስ በስልክ ቁጥር 202-387-4848 እንዲደውሉ እናበረታታቸዋለን።(የስልክ አገልግሎታችን ግን ከእኩለ ቀን 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 1፡00 ሰዓት ግን ይዘጋል)። የምንሰጠው አገልግሎት በሙሉ በስልክ ብቻ ነው።
  • በሜሪላንድ( MD) የሚገኙ ከቤተሰብ ሁከትና ረብሻ ( domestic violence)፣ ወሲባዊ በደል(sexual assault)፣ እና/ ወይም ድብያ የዳኑ ሰዎች፣ የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ ምክር ሲፈልጉ ወይም የህዝባዊ አገልግሎት ቀጠሮን በተመለከተ (ከ ቀኑ 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 1 ሰዓት በስተቀረ) ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 9:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 4:00 በስልክ ቁጥር 240-594-0600 ሊደውሉልን ይችላሉ። የምንሰጠው አገልግሎት ሁሉ በስልክ ብቻ ነው።
  • ወቅታዊ ደንበኞቻችን፡ ተጨማሪ መረጃ ሲያስፈልጋቸው፣ ጠበቆቻቸውን ወይም የህዝባዊ አገልግሎት ጉዳይ ተወካዮቻቸውን (case workers)በቀጥታ እንዲያገኙ እናበረታታለን። ለወቅታዊ ደንበኞቻችን አገልግሎት መስጠታችንን እየቀጥልን ነው።
  • ዩ-ኤስ-ሲ-አይ-ኤስ (የአሜሪካ የዜግነትና የስደተኞች ክፍል) (USCIS) በአካል ወደ ጽህፈት ቤቱ ከመጋቢት 18 እስከ ሚያዝያ አንድ ቀን ድረስ ለመምጣት የተደረጉ ቀጠሮዎችን በሙሉ ሰርዟል። ዌብሳይታችንን በየግዜው አዲስ መረጃ በመጨመር እናድሳለን። ስለዚህ ለወቅታዊ መረጃ ሁሌም የሚከተለውን ዌብሳይት ይጎብኙ፣ https://www.uscis.gov/about-us/uscis-response-coronavirus-disease-2019-covid-19.
  • በባልቲሞርና በአርሊንግተን የሚገኙ የስደተኞች ጉዳይ ፍርድቤቶች( በቁጥጥር ስር ያሉ ስደተኞች ጉዳይ በስተቀር) በፍርድቤት እንዲሰሙ እስከ ሚያዝያ 10 ቀን ቀጠሮ የተያዘላቸውን ለሌላ ቀን አስተላልፏል። አዲስ መረጃ ሲኖር ዌብሳይታችንን ቶሎ ቶሎ አ
  • እናድሳለን። ወቅታዊ ለሆነ የዩ-ኤስ-ሲ-አይ-ኤስ (የአሜሪካ የዜግነትና የስደተኞች ክፍል) (USCIS) መረጃ ግን https://www.justice.gov/eoir/eoir-operational-status-during-coronavirus-pandemic. ይጎብኙ።

አዩንዳ (Ayuda ) ቀደም ሲል በሚያዝያ ወር ላይ ይጀመራል ብሎ አድርጎት የነበረ የስደተኞችን የነጻ ምክር አገልግሎት በአሁኑ ግዜ ሰርዞታል። ነጻ የምክር አገልግሎት የምንሰጠው በ ግንቦት ወር ላይ ሲሆን ቀኑ እየደረሰ ሲመጣ አዲስ መረጃ እንሰጣለን